am_ezk_text_ulb/40/28.txt

1 line
996 B
Plaintext

\v 28 ቀጥሎም ሰውዬው ከሌላኛው በር እኩል ልኬት ባለው በደቡብ በር በኩል ወደ ውስጠኛው አደባባይ አገባኝ ። \v 29 የዘበኛ ጓዳዎቹንና የግንቡን አዕማድና መተላለፊያዎቹ ከመጀመሪያዎቹ መግቢያዎች እኩል ነበሩ፤ በመተላለፊያዎቹ ዙሪያ መስኮቶች ነበሩ።ውስጠኛው መግቢያና መተላለፊያው ርዝመቱ አምሳ ክንድ ወርዱም ሀያ አምስት ክንድ ነበረ። \v 30 በውስጠኛው ግንብ ዙሪያውም መተላለፊያዎች ነበሩ። ርዝመታቸውም ሀያ አምስት ክንድ ወርዳቸውም አምስት ክንድ ነበረ። \v 31 መተላለፊያዎቹም ወደ ውጭው አደባባይ ይመለከቱ ነበር በግንቡም አዕማድ ላይ የዘንባባ ዛፍ ተቀርጾ ነበር ወደ እርሱም የሚያደርሱ ስምንት ደረጃዎች ነበሩ።