am_ezk_text_ulb/40/11.txt

1 line
713 B
Plaintext

\v 11 ቀጥሎም ሰውዬው የበሩን መግቢያ ወርድ ለካ አሥር ክንድ ሆነ፤ የበሩንም መግቢያ ርዝመት ለካ አሥራ ሦስት ክንድ ሆነ። \v 12 በእያንዳንዱ በዘበኛ ጓዳ ፊት ከፍታው አንድ ክንድ የሆነ መከለያ ነበረ። የዘበኛ ጓዳዎቹም በሁሉም አቅጣጫ ስድስት ክንድ ከፍታ ነበራቸው። \v 13 ከአንዱም የዘበኛ ጓዳ ደርብ ጀምሮ እስከ ሌላው ደርብ ድረስ የበሩን ወርድ ሀያ አምስት ክንድ ለካ ይህም ከመጀምሪያው የዘበኞች ጓዳ መግቢያ እስከ ሌላኛው መግቢያ ድረስ ነው።