am_ezk_text_ulb/40/05.txt

1 line
938 B
Plaintext

\v 5 እነሆም፥ በቤተመቅደሱ ዙሪያው ቅጥር ነበረ፥ በሰውዬውም እጅ ርዝመቱ ስድስት ክንድ የሆነ የመለኪያ ዘንግ ነበር። እያንዳንዱም ክንድ አንድ ክንድ ከስንዝር ነበረ። ሰውዬውም ቅጥሩን ለካ፤ የቅጥሩም ስፋት አንድ ዘንግ ቁመቱንም አንድ ዘንግ ነበረ። \v 6 ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከተውም በር ሄዶ በደረጃዎቹ ወጣ፥ የመድረኩንም ወለል ለካ፥ ወርዱን አንድ ዘንግ ነበር። \v 7 የዘበኞቹም ጓዳ ሁሉ ርዝመቱ አንድ ዘንግ፥ ወርዱም አንድ ዘንግ ነበረ በዘበኞቹም ጓዳዎች መካከል አምስት ክንድ ርቀት ነበረ በበሩም ደጀ ሰላም በስተ ውስጥ በኩል የሚገኝ የበሩ የመድረክ ወለል አንድ ዘንግ ነበረ።