am_ezk_text_ulb/39/04.txt

1 line
559 B
Plaintext

\v 4 የአንተና የጭፍሮች ሁሉ ከአንተም ጋር ያሉ ሠራዊትና ወታደሮች ሬሳ ይገኛል። ለሚናጠቁ ወፎች ሁሉና ለምድር አራዊትም መብል አድርጌ እሰጥሃለሁ። \v 5 አንተ በምድር ፊት ላይ ትወድቃለህ እኔ ተናግሬአለሁና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። \v 6 በማጎግም ላይ ሳይፈሩም በደሴቶች በሚቀመጡ ላይ እሳትን እሰድዳለሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።