am_ezk_text_ulb/38/10.txt

1 line
773 B
Plaintext

\v 10 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚያ ቀን በልብህ ታቅዳለህ፥ \v 11 ክፉ አሳብንም ታስባለህ።' እንዲህም ትላለህ፥ 'ቅጥር ወደሌላቸው መንደሮች እወጣለሁ ተዘልለው ወደሚኖሩ፥ ሁላቸው ሳይፈሩ ያለ ቅጥርና ያለ መወርወሪያ ያለ መዝጊያም ወደሚቀመጡ እገባለሁ \v 12 ባድማም በነበሩና በቅርቡ ሰዎች በሚኖሩባቸው ስፍራዎች ላይ፥ ከብትና ዕቃንም ይዘው ከአሕዛብም በተሰበሰቡ ሰዎች በምድርም መካከል በሚኖሩ ሕዝብ ላይ እጄን እዘረጋናምርኮን እማርካለሁ ብዝበዛንም እበዘብዛለሁ ።