am_ezk_text_ulb/38/07.txt

1 line
794 B
Plaintext

\v 7 ተዘጋጅ! አዎ፥ ራስህንና ሠራዊትህን አዘጋጅ አለቃም ሁናቸው። \v 8 ከብዙ ቀናትም በኋላ ትጠራልህ ክተወሰኑ ዓመታት በኋላ ክሠይፍ እያገገመች ወዳለችው፥ ከብዙ ሕዝቦችም መካከል ተሰብስበው ያለማቋረጥ ባድማ በነበሩት በእስራኤል ተራሮች ላይ ዳግም ወደ ተሰበሰቡ ትሄዳለህ። የምድሪቱ ሕዝብ ግን ከሕዝቦች መካከል ወጥተው ሁሉም ሳይፈሩ ይቀመጡባታል። \v 9 አንተም ትወጣለህ፥ እንደ ዐወሎ ነፋስም ትመጣለህ አንተና ጭፍሮችህ ሁሉ ከአንተም ጋር ብዙ ሕዝብ ምድሪቱን እንደ ደመና ትሸፍናላችሁ።