am_ezk_text_ulb/37/04.txt

1 line
729 B
Plaintext

\v 4 እርሱም እንዲህ አለኝ፥ "በእነዚህ አጥንቶች ላይ ትንቢት ተናገር እንዲህም በላቸው፥ 'እናንተ የደረቃችሁ አጥንቶች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ሰሙ። \v 5 ጌታ እግዚአብሔር ለእነዚህ አጥንቶች እንዲህ ይላል። እነሆ፥ መንፈስን አገባባችኋለሁ በሕይወትም ትኖራላችሁ። \v 6 ጅማትም እሰጣችኋለሁ ሥጋንም አወጣባችኋለሁ በእናንተም ላይ ቁርበትን እዘረጋለሁ ትንፋሽንም አገባባችኋለሁ በሕይወትም ትኖራላችሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።