am_ezk_text_ulb/36/10.txt

1 line
909 B
Plaintext

\v 10 ስለዚህም እናንተ ተራሮች ሆይ በእስራኤል ቤት ሁሉ ሰዎችን አበዛባችኋለሁ። ሁሉም! ከተሞች የሰዎች መኖሪያ ይሆናሉ ባድማዎቹም ስፍራዎች ይሠራሉ። \v 11 እናንተ ተራሮች ሆይ ሰውንና እንስሳውንም አበዛባችኋለሁ፥ እነርሱም ይበዛሉ ያፈሩማል። ቀድሞ እንደነበራችሁት የሰዎች መኖሪያ አደርጋችኋለሁ፥ ከቀድሞ ይልቅ አበለጥጋችኋለሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ። \v 12 በእናንተ ላይ እንዲረማመዱ የሕዝቤን የእስራኤልን ሰዎችን አመጣቸዋለሁ። እነርሱም ይወርሱዋቸዋል ርስትም ትሆኑላቸዋላችሁ፥ ከእንግዲህም የልጆቻቸው ሞት ምክንያት አትሆኑም።