\v 8 እናንተ የእስራኤል ተራሮች ግን ወደ እናንተ ተመልሰው የሚመጡበት ቀን ቀርቧልና፥ ቅርንጫፎቻችሁን ታቈጠቍጣላችሁ፥ ለሕዝቤ ለእስራኤልም ፍሬአቸሁን ትሰጣላችሁ። \v 9 እነሆ፥ እኔ ለእናንተ ነኝና ወደ እናንተም እመለከታለሁ፥ እናንተም ትታረሳላችሁ ይዘራባችሁማል።