am_ezk_text_ulb/34/25.txt

1 line
799 B
Plaintext

\v 25 የሰላምን ቃል ኪዳን ከእነርሱ ጋር እገባለሁ ክፉዎችንም አራዊት ከምድሪቱ አጠፋለሁ፥ በጎቼም ተጠብቀው በምድረ በዳ ይኖራሉ በዱርም ውስጥ ይተኛሉ። \v 26 በእነርሱና በዙሪያ ባሉ ኮረብቶቼ በረከቴን አፈሳለሁ፥ ዝናቡንም በጊዜው እልካለሁ። ይህም የበረከት ዝናብ ይሆናል። \v 27 የምድረ በዳም ዛፍ ፍሬውን ይሰጣል ምድርም ቡቃያዋን ትሰጣለች፥ በጎቼ በምድራቸው ተዘልለው ይኖራሉ የቀንበራቸውንም ማነቆ በሰበርሁ ጊዜ ከሚገዙአቸውም እጅ ባዳንኋቸው ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።