am_ezk_text_ulb/34/04.txt

1 line
647 B
Plaintext

\v 4 የደከመውን አላጸናችሁትም የታመመውንም አላከማችሁትም የተሰበረውንም አልጠገናችሁትም የባዘነውንም አልመለሳችሁትም የጠፋውንም አልፈለጋችሁትም በኃይልና በጭቈናም ገዛችኋቸው። \v 5 ያለ እረኛም በማጣት ተበተኑ፥ ከተበተኑም በኋላ ለምድር አራዊት ሁሉ መብል ሆኑ። \v 6 በጎቼ በተራሮች ሁሉና በረዘሙ ኮረብቶች ሁሉ ላይ ተቅበዝብዘዋል፥ በምድርም ፊት ሁሉ ላይ ተበትነዋል። የሚፈልጋቸውም የለም።