am_ezk_text_ulb/33/07.txt

1 line
735 B
Plaintext

\v 7 አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ለእስራኤል ቤት ጕበኛ አድርጌሃለሁ፤ ከአፌ ቃሌን ስማ እኔን ወክለህ አስጠንቅቃቸው። \v 8 ኃጢአተኛውን "ኃጢአተኛ ሆይ፥ በእርግጥ ትሞታለህ!" ባልኩት ጊዜ፥ ኃጢአተኛውን ከመንገዱ እንዲመለስ ለማስጠንቀቅ ባትናገር ያ ኃጢአተኛ በኃጢአቱ ይሞታል፥ ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ። \v 9 ነገር ግን ከመንገዱ እንዲመለስ ኃጢአተኛውን ብታስጠነቅቀው እርሱ ግን ከመንገዱ ባይመለስ በኃጢአቱ ይሞታል አንተ ግን ነፍስህን አድነሃል።