am_ezk_text_ulb/32/24.txt

1 line
868 B
Plaintext

\v 24 ኤላምም ከአገልጋዮቿ ጋር በዚያ አለች፤ መቃብሮቿም ከበዋታል። ሁሉም የተገደሉ ናቸው። እነርሱም በሕያዋን ምድር ያስፈሩ ሁሉ ፥ ሳይገረዙም ወደ ታችኛው ምድር የወረዱ፥ በህያዋን ምድር ሽብርን ያመጡና ወደ ጕድጓድም ከሚወርዱ ጋር እፍረታቸውን የተሸከሙ ናቸው። \v 25 በተገደሉት መካከል ለኤላምና ለአገልጋዮቻ መኝታን አድርገውላታል፤ መቃብርዋ በዙሪያዋ ነው! ሁሉም ያልተገረዙና በህያዋን ምድር ሽብርን በማምጣታቸው በሰይፍ የተገደሉ ናቸው! ወደ ጕድጓድም ከሚወርዱ ጋር እፍረታቸውን ተሸክመዋል። ኤላምም በተገደሉትም መካከል ነች።