am_ezk_text_ulb/32/01.txt

1 line
592 B
Plaintext

\c 32 \v 1 እንዲህም ሆነ በአሥራ ሁለተኛው ዓመት በአሥራ ሁለተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ። \v 2 የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለ ግብጽ ንጉሥ ስለ ፈርዖን ሙሾ አሙሽ፥ እንዲህም በለው፥ 'በእህዛብ መካከል እንደ አንበሳ ደቦል በባህር እንዳለ አስፈሪ ፍጥረት ነበርክ፤ ውሃውን አናወጥከው፥ ውሆችን በእግርህ በጥብጠህ አጨቀየሀቸው።