am_ezk_text_ulb/31/13.txt

1 line
638 B
Plaintext

\v 13 የሰማይ ወፎች ሁሉ በግንዱ ላይ ይቀመጣሉ የምድርም አራዊት ሁሉ በቅርንጫፎቹ ላይ ይቀመጣሉ። \v 14 ይህም የሆነው ወደ ጕድጓድ በሚወርዱ በሰው ልጆች መካከል ሁላቸው ለታችኛው ምድር ለሞት አልፈው ተሰጥተዋልና ውሀ ሲጠጡ ከነበሩት ዛፎች ውስጥ አንዳቸውም ረጅም ሆነው እንዳያድጉ፥ ጫፎቻቸውም ከቅጠሎች በላይ እንዳይሆኑ፥ በውኃ አጠገብ ያሉ ዛፎች ሁሉ ከእንግዲህ በቁመታቸው እንዳይረዝሙ ነው።