am_ezk_text_ulb/31/05.txt

1 line
529 B
Plaintext

\v 5 ቁመቱ ከምድረ በዳ ዛፍ ሁሉ ከፍ ያለ ነበር አለ፤ ቅርንጫፎቹም ከብዙ ውኆች የተነሣ ረዘሙ። \v 6 የሰማይ ወፎች ሁሉ ጎጆቻቸውን በቅርንጫፎቹ ላይ አደረጉ፥ የምድርም አራዊት ሁሉ ከጥላው በታች ተዋለዱ። ታላላቅ ህዝቦች ከጥላውም በታች ኖሩ። \v 7 ሥሩም በብዙ ውኃ አጠገብ ነበረና በታላቅነቱና በቅርንጫፎቹ ርዝመት የተዋበ ነበረ።