am_ezk_text_ulb/30/22.txt

1 line
653 B
Plaintext

\v 22 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ እኔ በግብጽ ንጉሥ በፈርዖን ላይ ተነስቻለሁ! ጠንካራውንም የተሰበረውንም ክንዱን እሰብራለሁ፥ ሰይፉንም ከእጁ አስጥላለሁ። \v 23 ግብጻውያንንም ወደ አሕዛብ እበትናለሁ ወደ አገሮችም እዘራቸዋለሁ። \v 24 የፈርዖንን ክንድ ለመስበር የባቢሎንን ንጉሥ ክንድ አበረታለሁ ሰይፌንም በእጁ እሰጣለሁ። በባቢሎን ንጉሥ ፊት ለሞት እንድሚያጣጥር ሰው ያጓራል።