am_ezk_text_ulb/30/13.txt

1 line
482 B
Plaintext

\v 13 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጣዖቶችን አጠፋለሁ እርባና ቢስ የሆኑትን የሜምፎስ ጣዖታት እሽራለሁ። ከእንግዲህ ወዲያ በግብጽ ምድር አለቃ አይገኝም ፥ በግብጽም ምድር ላይ ሽብርን አደርጋለሁ! \v 14 ጳትሮስንም አፈርሳለሁ፥ በጣኔዎስም እሳትን አነድዳለሁ፥ በኖእ ላይም ፍርድን አደርጋለሁ።