\v 10 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ የግብጽን ህዝብ ፍጻሜ አመጣለሁ። \v 11 የአህዛብ ድንጋጤ የሆኑት እርሱና ሠራዊቱ ምድሪቱን ለማጥፋት ይመጣሉ፤ ሰይፋቸውንም በግብጽ ላይ ይመዝዛሉ ምድሪቱንም በሞቱ ሰዎች ይሞላሉ!