\v 6 ለእስራኤል ቤት የሸንበቆ በትር ሆነዋልና በግብጽም የሚኖሩ ሁሉ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ። \v 7 በእጅ በያዙህ ጊዜ ተሰበርህና ተሰነጣጥቅህ ትከሻቸውን ትወጋለህ፤ በተደገፉብህም ጊዜ እግራቸውን ትሰባብራለህ ወገባቸውንም እንዲንቀጠቀጥ ታደርጋለህ።