\v 18 በበደልህ ብዛት ቅን ባልሆነው ንግድህም ቅዱስ ስፍራህን አረከስህ! ስለዚህ እሳትን ከውስጥህ አውጥቻለሁ እርስዋም ትበላሀለች። በሚያዩህም ሁሉ ፊት በምድር ላይ አመድ አደርግሀለሁ። \v 19 በአሕዛብም ውስጥ የሚያውቁህ ሁሉ ይደነቁብሃል፤ ይደነግጣሉ ፥ አንተም እስከ ዘላለምም አትገኝም።