am_ezk_text_ulb/28/11.txt

1 line
885 B
Plaintext

\v 11 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ። \v 12 የሰው ልጅ ሆይ፥ በጢሮስ ንጉሥ ላይ ሙሾ አሞሽተህ እንዲህ በለው፥ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡ጥበብን የተሞላህ የፍጽምና መደምደሚያ በውበትህም ፍጹም ነበርክ! \v 13 በእግዚአብሔር ገነት በዔድን ነበርህ! በከበረ ዕንቍስ ሁሉ፥ ሰርድዮን፥ ቶጳዝዮን፥ አልማዝ፥ ቢረሌ፥ መረግድ፥ ኢያስጲድ፥ ሰንፔር፥ በሉር፥ የሚያብረቀርቅ ዕንቍ፥ ወርቅ፥ ተሽፍነህ ነበረ። እነዚህ የከበሩ ድንጋዮች በወርቅ ዕቃ በፊትህ ተቀምጠው ነበር። አነዚህም በተፈጠርህበት ቀን እንድትለብሳቸው ተዘጋጅተው ነበር!