am_ezk_text_ulb/27/31.txt

1 line
601 B
Plaintext

\v 31 ስለ አንቺም የራሳቸውን ጠጕር ይላጫሉ ማቅም ይታጠቃሉ በምሬትም ስለአንቺ ያነባሉ ይጮኸሉ። \v 32 በትካዜያቸውም ልቅሶ ያነሡልሻል፥ ስለ አንቺም ሙሾ ያሞሻሉ እንዲህም ይላሉ። በባሕር መካከል ጠፍቶ እንደ ቀረ እንደ ጢሮስ ያለ ማን ነው? \v 33 ሸቀጥሽ ከባሕር በወጣ ጊዜ ብዙ አሕዛብን ያጠግብ ነበር በብልጥግናሽና በንግድሽ ብዛት የምድርን ነገሥታት ባለ ጠጎች አድርገሻል።