\v 22 የሳባና የራዕማ ነጋዴዎች ምርጥ የሆነ የቅመም ሽቱ ሁሉና ብዙ ዓይነት የከበሩ ድንጋዮች ሊሸጡልሽ ይመጡ ነበር። ወርቅም ይነግዱ ነበር። \v 23 ካራንና ካኔ ዔድንም ከሳባ፥ ከአሦርና ከኪልማድ በመሆን የንግድ አጋሮችሽ ነበሩ።