\v 6 ከባሳን ዛፍ መቅዘፊያሽን ሠርተዋል፥ በዝሆን ጥርስ ከታሸበ ከኪቲም ደሴቶች ዛፍ የመርከብ ወለሎችሽን ሠርተዋል። \v 7 የመርከብሽ ሸራ ልክ እንደ ሰንደቅ ዓላማሽ የግብጽ ባለብዙ ቀለማት በፍታ ጨርቆች ነበሩ።