|
\v 15 ጌታ እግዚአብሔር ጢሮስን እንዲህ ይላታል፥ ' በውስጥሽ እልቂት በሆነ ጊዜ በውድቀትሽ ጩኸትና በቆሰሉ ሰዎች የሥቃይ ድምጽ የተወጉት ባንቋረሩ ጊዜ፥ ፥ ከውድቀትሽ ድምፅ የተነሣ ደሴቶች አይነዋወጡምን? \v 16 የባሕርም አለቆች ሁሉ ከዙፋኖቻቸው ይወርዳሉ መጐናጸፊያቸውን ያወጣሉ ወርቀ ዘቦ ልብሳቸውንም ያወልቃሉ መንቀጥቀጥን ለብሰው በመሬት ላይ ይቀመጣሉ፥ ሁልጊዜም ይንቀጠቀጣሉ ስለአንቺም ይፈራሉ። |