am_ezk_text_ulb/26/09.txt

1 line
657 B
Plaintext

\v 9 ማፍረሻውን በቅጥርሽ ላይ ያደርጋል፥ መሳሪያውም ግንቦችሽንም ያፈርሳል! \v 10 ከፈረሶቹም ብዛት የተነሣ ትቢያቸው ይከድንሻል! ሰዎችም በፈርሰ ቅጥር በኩል ወደ ከተማ እንደሚገቡ እርሱ በበሮችሽ ሲገባ፥ ከፈረሰኞችና ከመንኰራኵሮች ከሰረገሎችም ድምፅ የተነሣ ቅጥርሽ ይናወጣል። \v 11 በፈረሶቹ ኮቴ ጎዳናዎችሽን ሁሉ ይረመርማል፤ ሕዝብሽንም በሰይፍ ይገድላል፥ የብርታትሽም ሐውልት ወደ ምድር ይወድቃል።