am_ezk_text_ulb/25/08.txt

1 line
808 B
Plaintext

\v 8 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ 'ሞዓብና ሴይር እነሆ፥ "የይሁዳ ቤት ያው እንደ ሌሎቹ አሕዛብ ሁሉ ነው!" ብለዋልና \v 9 ስለዚህ፥ እነሆ፥ የሞዓብን ጫንቃ ከከተሞቹ፥ በዳርቻው ካሉት የምድሩ ትምክሕት ከሆኑት ከተሞቹ፥ ከቤትየሺሞት፥ ከበኣልሜዎን፥ \v 10 ከቂርያታይም፥ ከአሞን ልጆች ጋር ለምሥራቅ ልጆች እከፍታለሁ። የአሞን ህዝብ በአሕዛብ መካከል ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይታሰቡ ርስት አድርጌ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ። \v 11 በሞዓብም ላይ ፍርድን አደርጋለሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።