am_ezk_text_ulb/25/03.txt

1 line
931 B
Plaintext

\v 3 ለአሞንም ሰዎች እንዲህ በል፥ 'የጌታን የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡ መቅደሴ በረከሰ ጊዜ የእስራኤልም ምድር ባድማ በሆነች ጊዜ የይሁዳም ቤት በተማረኩ ጊዜ ስለ እነርሱ "እሰይ!" ብላችኋል። \v 4 ስለዚህ፥ እነሆ፥ ርስት አድርጌ ለምሥራቅ ሰዎች ርስት አድርጌ አሳልፌ አሰጣችኋለሁ፥ እነርሱም በእናንተ ላይ ምሽግን ይሰራሉ ፥ ድንኳኖቻቸውንም በእናንተ ዘንድ ይተክላሉ። ፍሬያችሁን ይበላሉ ወተታችሁንም ይጠጣሉ! \v 5 የአሞንን ከተማ ለግመሎች ማሰማርያ፥ የአሞንንም ልጆች ለመንጋ መመሰጊያ አደርጋለሁ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።