am_ezk_text_ulb/24/22.txt

1 line
712 B
Plaintext

\v 22 እኔም እንዳደረግሁ እናንተ ታደርጋላችሁ ጢማችሁን አትሸፍኑም የኃዘንተኛ ሰዎችንም እንጀራ አትበሉም! \v 23 ይልቁኑ መጠምጠሚያችሁም በራሳችሁ ጫማችሁም በእግራችሁ ይሆናል፤ አታዝኑም ወይም አታለቅሱምም በኃጢአታችሁም ትሰለስላላችሁና እያንዳንዱ ሰው ስለወንድሙ ያቃስታል። \v 24 ይህ በሚሆንባችሁ ጊዜ ሕዝቅኤልም ምልክት ይሆናችኋል እርሱ እንዳደረገ ሁሉ እናንተ ታደርጋላችሁ። ከዚያም እኔ ጌታ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።