am_ezk_text_ulb/24/19.txt

1 line
626 B
Plaintext

\v 19 ሕዝቡም፥ "ይህ የምታደርገው ነገር ምን እንደ ሆነ አትነግረንምን?" አሉኝ። \v 20 እኔም እንዲህ አልኋቸው፥ "የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥ \v 21 ለእስራኤል ቤት ተናገር እንዲህም በል፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የኃይላችሁ ትምክሕት፥ የዓይናችሁ አምሮት፥ ክፉ ምኞታችሁ መቅደሴን አርክሰዋል! ያስቀራችኋቸውም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ።