\v 36 እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፥ "የሰው ልጅ ሆይ፥ በኦሖላና በኦሖሊባ ትፈርዳለህን? እንግዲያውስ አሳፋሪ ተግባራቸውን አስታውቃቸው \v 37 አመንዝረዋልና፥ ደምም በእጃቸው አለና! ከጣዖቶቻቸውም ጋር አመንዝረዋልና፥ ለእኔም የወለዱአቸውን ልጆቻቸውን ለእሳት መቃጠል አሳልፈዋቸዋልና።