\v 26 ልብስሽንም ይገፍፉሻል ጌጣጌጥሽንም ይወስዳሉ! \v 27 አሳፋሪ ባህሪሽን፥ ከግብጽ ምድር ያመጣሽውን ግልሙትናሽንም ከአንቺ አስወግዳለሁ። ዓይንሽንም ወደ እነርሱ በናፍቆት አታነሺም ግብጽንም ከዚያ ወዲያ አታስቢም።