\v 18 ግልሙትናዋንም ገለጠች ኅፍረተ ሥጋዋንም አሳየች ነፍሴም ከእኅትዋ እንደ ተለየች እንዲሁ ነፍሴ ከእርስዋ ተለየች። \v 19 ነገር ግን በግብጽ ምድር የገለሞተችበትን የኰረዳነትዋን ዘመን በማሰላሰል ግልሙትናዋን አበዛች።