\v 16 ባየቻቸውም ጊዜ ለክፉ ተመኘቻቸው፥ ወደ ከላውዴዎን ምድር ወደ እነርሱ መልእክተኞችን ላከች። \v 17 የባቢሎንም ሰዎች ወደ እርስዋ ወደ ሴሰኝነት መኝታ መጡ በግልሙትናቸውም አረከሱአት እርስዋም ከእነርሱ ጋር ረከሰች በውርደትም ከእነርሱ ተለየች።