\v 14 ግልሙትናዋንም አበዛች! በቀይ ቀለምም የተሳለውን የከለዳውያንን ስዕል፥ በግድግዳ ላይ የተሳሉትን ሰዎች አየች። \v 15 በወገባቸው ዝናር የታጠቁ ራሳቸውንም በቀለማዊ መጠምጠሚያ የጠመጠሙ ነበሩ! ሁሉም የከለዳዊያን ተወላጆችና የሠረገላ አዛዦች ይመስሉ ነበር።