am_ezk_text_ulb/23/08.txt

1 line
690 B
Plaintext

\v 8 በግብጽም የነበረውን ግልሙትናዋን አልተወችም በዚያ በኰረዳነትዋ ጊዜ ከእርስዋ ጋር ተኝተው ነበር፥ የድንግልናዋንም ጡቶች ዳብሰው ነበር፥ ግልሙትናቸውንም አፍስሰውባት ነበር። \v 9 ስለዚህ በፍቅር በተከተለቻቸው በውሽሞችዋ በአሦራውያን እጅ አሳልፌ ሰጠኋት። \v 10 እነርሱም ኅፍረተ ሥጋዋን ገለጡ ወንዶችና ሴቶች ልጆችዋንም ማርከው ወሰዱ፥ እርስዋንም በሰይፍ ገደሉ በሌሎች ሴቶች ዘንድ መተረቻ ሆነች ስለዚህም ፈረዱባት።