am_ezk_text_ulb/23/05.txt

1 line
597 B
Plaintext

\v 5 ኦሖላም የእኔ ሆና እያለ ገለሞተችብኝ፤ ውሽሞችዋንም ኃያላኑን ጎረቤቶችዋን አሦራውያንን በሴሰኝነት ተከተለቻቸው። \v 6 እነርሱም ሰማያዊ ሐር የለበሱ አለቆችና ሹማምቶች፥ መልከ መልካሞች ጐበዛዝት፥ በፈረስ ላይ የሚቀመጡ ፈረሰኞች ነበሩ። \v 7 ስለዚህ ራሷን ለተመረጡ ለአሦር ሰዎች ሁሉ ለግልሙትና ሰጠቻቸው ፥ በሴሰኝነት በተከተለቻቸውም ጣዖቶቻቸው ሁሉ ረከሰች።