am_ezk_text_ulb/23/01.txt

1 line
667 B
Plaintext

\c 23 \v 1 የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥ \v 2 የሰው ልጅ ሆይ፥ የአንዲት እናት ልጆች የሆኑ ሁለት ሴቶች ነበሩ። \v 3 በግብጽ አገር በኰረዳነታቸው ዕድሜ አመነዘሩ በዚያ ገለሞቱ። በዚያ ጡቶቻቸው ምዋሸሹ በዚያም የድንግልናቸው ጡቶች ተዳበሱ። \v 4 ስማቸውም የታላቂቱ ኦሖላ የታናሽ እኅትዋም ኦሖሊባ ነበረ። ለእኔም ሆኑ ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለዱ። ኦሖላ ሰማርያ ናት ኦሖሊባ ደግሞ ኢየሩሳሌም ናት።