am_ezk_text_ulb/22/26.txt

1 line
858 B
Plaintext

\v 26 ካህናቶችዋም ሕጌን አቃለዋል ቅድሳቴንም አርክሰዋል። ቅዱስ በሆነና ቅዱስ ባልሆነ መካከልም አይለዩም፥ በንጹሕና በርኩስ መካከል ያለውን ልዩነት አያስተምሩም። ፊታቸውንም ከሰንበታቴ መለሱ እኔም በመካከላቸው ረከስሁ። \v 27 በውስጥዋ ያሉ አለቆችዋ እንደሚናጠቁ ተኵላዎች ናቸው። የስስትን ትርፍ ለማግኘት ሲሉ ደምን ያፈሳሉ ህይወትንም ያጠፋሉ። \v 28 እግዚአብሔርም ሳይናገር ነቢያቶችዋ፥ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል" እያሉ ከንቱን ራእይ በማየት የሐሰትንም ምዋርት ለእነርሱ በማምዋረት ያለ ገለባ በጭቃ ይመርጓቸዋል።