am_ezk_text_ulb/22/20.txt

1 line
778 B
Plaintext

\v 20 እንዲያቀልጡት እሳት ያናፉበት ዘንድ ብርንና መዳብን ብረትንና እርሳስን ቈርቈሮንም በከውር እንደሚሰበስቡ፥ እንዲሁ አቀልጣችኋለሁ። ስለዚህ በቍጣዬና በመዓቴ እሰበስባችኋለሁ፥ በዚያም ውስጥ እጨምራችኋለሁ እሳትም አናፋባችኋለሁ አቀልጣችሁማለሁ። \v 21 ስለዚህም አሰበስባችሁማለሁ የመዓቴንም እሳት አናፋባችኋለሁ በውስጡም ትቀልጣላችሁ። \v 22 ብርም በማቅለጫ ውስጥ እንደሚቀልጥ፥ እንዲሁ በውስጧ ትቀልጣላችሁ እኔም እግዚአብሔር መዓቴን እንዳፈሰስሁባችሁ ታውቃላችሁ።