am_ezk_text_ulb/22/06.txt

1 line
656 B
Plaintext

\v 6 እነሆ፥ የእስራኤል አለቆች እያንዳንዳቸው በኃይላቸው መጠን ደም ያፈስሱ ዘንድ በአንቺ ውስጥ ነበሩ። \v 7 በውስጥሽ አባቶችንና እናቶችም አቃለሉ፥ በመካከልሽ በመጻተኛው ላይ በደልን አደረጉ። በአንቺ ውስጥ ድሀ አደጉንና መበለቲቱን አስጨነቁ። \v 8 ቅዱሳቴንም ናቅሽ ሰንበታቴንም አረከስሽ! \v 9 ደምን ያፈስሱ ዘንድ ቀማኞች ሰዎች በአንቺ ውስጥ ነበሩ በተራሮችም ላይ በሉ። በመካከልሽ ክፋትን አደረጉ።