am_ezk_text_ulb/21/21.txt

1 line
933 B
Plaintext

\v 21 የባቢሎን ንጉሥ የጥንቆላ ምሪት ለማግኘት በመንታ መንገድ መታጠፊያ ላይ ይቆማል። ፍላጾችን ይወዘውዛል፥ ከጣዖታቱም ምሪት ይጠይቃል። ጉበትም ይመለከታል። \v 22 የቅጥሩን ማፍረሻ ያደርግ ዘንድ፥ አፍንም በጩኸት ይከፍት ዘንድ፥ በውካታም ድምፅን ከፍ ያደርግ ዘንድ፥ የቅጥሩን ማፍረሻ በበሮች ላይ ያደርግ ዘንድ፥ አፈርን ይደለድል ዘንድ፥ ምሽግም ይሠራ ዘንድ የኢየሩሳሌም ዕጣ በቀኝ እጁ ውስጥ ነበረ። \v 23 በኢየሩሳሌም ላሉ ለባቢሎናዊያን መሐላን ማሉ ዓይን ፊት የሐሰት ምዋርት ይመስላል፥ ነገር ግን ንጉሱ እንዲያዙ ለማድረግ ስምምነታችሁን አፍርሳችኋል ብሎ ይከሳቸዋል።