am_ezk_text_ulb/21/06.txt

1 line
612 B
Plaintext

\v 6 ስለዚህም፥ አንተ የሰው ልጅ ሆይ፥ አልቅስ ወገብህን በማጕበጥ በፊታቸው ምርር ብለህ አልቅስ። \v 7 እነርሱም 'ስለ ምን ታለቅሳለህ?' ብለው ይጠይቁሀል፥ አንተም እንዲህ ትላቸዋለህ፥ 'ስለሚምጣው ክፉ ዜና ነው፥ ምክንያቱም ልብ ሁሉ ይቀልጣል፥ እጆችም ሁሉ ይዝላሉ፥ ነፍስም ሁሉ ትደክማለች፥ ጉልበትም እንደ ውኃ ይፈስሳል። እነሆ፥ ይመጣል ይፈጸምማል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር'"