\v 4 እኔም ጻድቁንና ክፉውን ከእናንተ ዘንድ ስለማጠፋ፥ ሰይፌ ከደቡብ ጀምሮ እስከ ሰሜን ድረስ ባለ በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ ከሰገባው ይመዘዛል። \v 5 ሥጋ ለባሹም ሁሉ እኔ እግዚአብሔር ሰይፌን ከሰገባው እንደ መዘዝሁ ያውቃል፥ ስይፌም ከእንግዲህ አይመለስም!