am_ezk_text_ulb/20/45.txt

1 line
714 B
Plaintext

\v 45 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፥ \v 46 "የሰው ልጅ ሆይ፥ ፊትህን ወደ ደቡብ አቅና በደቡብ ላይ ተናገር፤ በኔጌብ ዱር ላይ ትንቢት ተናገር \v 47 ለኔጌብም ዱር፥ 'የእግዚአብሔርን ቃል ስማ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በአንተ ውስጥ እሳት አነድዳለሁ። በውስጥህም ያለውን የለመለመውንና የደረቀውን ዛፍ ሁሉ ይበላል። የሚንበለበለው እሳትም አይጠፋም፤ ከደቡብም ጀምሮ እስከ ሰሜን ድረስ ያለው ገጽታ ሁሉ ይቃጠላል።