am_ezk_text_ulb/20/40.txt

1 line
637 B
Plaintext

\v 40 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል- በቅዱሱ ተራራዬ፥ ከፍ ባለው በእስራኤል ተራራ ላይ፥ በዚያ የእስራኤል ቤት ሁሉ ሁላቸው በምድራቸው ያመልኩኛል። በዚያም ቍርባናችሁን በኵራታችሁንም የቀደሳችሁትንም ነገር ሁሉ በደስታ እቀበላለሁ። \v 41 ከአሕዛብም ዘንድ ባወጣኋችሁ ጊዜ ከተበተናችሁባትም አገር ሁሉ በሰበሰብኋችሁ ጊዜ እንደ ጣፋጭ ሽታ እቀበላችኋለሁ፥ በአሕዛብም ፊት እቀደስባችኋለሁ።