am_ezk_text_ulb/20/27.txt

1 line
950 B
Plaintext

\v 27 ስለዚህ፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ለእስራኤል ቤት ተናገር፥ እንዲህም በላቸው፥ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡ በዚህም ደግሞ አባቶቻችሁ ባደረጉት ዓመፅ አስቈጡኝ። \v 28 እሰጣቸውም ዘንድ ወደ ማልሁላቸው ምድር ባገባኋቸው ጊዜ፥ በኮረብታ ላይ ያለውን የጣዖት ማምለኪያ ሁሉና ቅጠልማውንም ዛፍ ባዩ ጊዜ፥ በዚያ መሥዋዕታቸውን ሠዉ በዚያም የሚያስቈጣኝን ቍርባናቸውን አቀረቡ። በዚያም ደግሞ ጣፋጩን ሽታቸውን አደረጉ በዚያም የመጠጥ ቍርባናቸውን አፈሰሱ። \v 29 እኔም፥ "እናንተ ወደ እርሱ የምትሄዱበት ኮረብታማ ሥፍራ ምንድር ነው?" አልኋቸው። እስከ ዛሬም ድረስ ስሙ ባማ ተብሎ ተጠርቶአል።