\v 8 እነርሱ ግን ዐመፁብኝ ሊሰሙኝም አልወደዱም። እያንዳንዱ ርኩስ ነገሮችን ከአይኑ ፊት አላስወገደም የግብጽንም ጣዖታት አልተወም በዚህም ጊዜ። በግብጽ ምድር መካከል ቍጣዬን ልፈጽምባቸው መዓቴንም ላፈስባቸው ወሰንኩ። \v 9 ነገር ግን በመካከላቸው በሚኖሩበት ህዝብ መካከል እንዳይረክስ ስለ ስሜ ሰራሁ። ከግብጽ ምድር በማውጣት ራሴን በአይናቸው ፊት ገለጥኩላቸው።