am_ezk_text_ulb/19/01.txt

1 line
631 B
Plaintext

\c 19 \v 1 አንተም በእስራኤል አለቆች ላይ ይህን ሙሾ አሙሽ፥ እንዲህም በል፥ \v 2 'እናትህ ማን ነበረች? አንበሳ ነበረች ከአንበሳ ደቦል ጋር ተጋደመች ግልገሎችዋን አሳደገች። \v 3 ከግልገሎችዋም አንዱን ደቦል አንበሳ እንዲሆንና ጠላቶቹን የሚቆራርጥ እንዲሆን አሳደገችው። ሰዎችንም በላ። \v 4 አሕዛብም ወሬውን ሰሙ እርሱም በወጥመዳቸው ተያዘ፥ በሰንሰለትም አድርገው ወደ ግብጽ ምድር ወሰዱት።